Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: በጋሞ ጎፋ ዞን ዲታ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-07-03

 

Tender Detail:

 




በጋሞ ጎፋ ዞን በዲታ ወረዳ ለሚያስገነባው የትምህርት ቢሮ ግንባታ በ2008 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ደረጃው BC/GC 6 ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮች ሆነው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በስራና ከተማ ልማት ሚ/ር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች መሆን ይኖርባቸዋል፣
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችንና መሳሪያዎች በግላቸው አጓጉዘው የሚሰሩ መሆን አለባቸው፣
  3. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 30,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በጥሬ ገንዘብ ወይም ባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  4. ተጫራቾች ሕጋዊ ፈቃዳቸውንና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት በማቅረብ የጨረታውን ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በዲታ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብና በመክፈል የከፈሉትን ወይም ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፣
  5. ማንኛውም ተጫራች ከወድድሩ በፊት የስራ ሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ ማረጋገጥ ይችላል፣
  6. የፋናንሻል ጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናል ሁለት ፎቶ ግራፍ ኮፒው በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት በሁለቱም ፖስታዎች ላይ ስም አድራሻና የፕሮጀክቱ ስም በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም በታሸገ አንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና እላዩ በተዘረዘሩ ጽሑፎች እላዩ ላይ በመፃፍ ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዲታ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  7. የጨረታው ሳጥን የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ስራ ቀን ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
  8. የጨረታው ማስከበሪያ (Bid Bond)  ፋይናንሻል ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ ተካቶ መቅረብ አለበት፣
  9. በወረዳው ውስጥ የግንባታ ስራ ላይ ያለ ተቋራጭ ድርጅት ስለ መጨረሱ ከሚሰራበት ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ ካላመጣ የማይወዳደር መሆኑን እንገልፃለን፣
  10. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፣

ስልክ ቁጥር 09 16 46 76 97/ 09 10 92 83 61

        በጋሞ ጎፋ ዞን ዲታ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት