Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት

Dead Line: 2016-08-20

 

Tender Detail:

 




የአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ለሚገኙት ለህግ ታራሚዎች ጥሬ የምግብ እህልና የበሰለ ምግብ የተለያዩ ማጣፈጫዎችን አንዲሁም የማገዶ እንጨት ከነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 (አምስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀምና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ማንኛውም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡-

  1. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የ2008 ዓ.ም የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ይጠበቅባቸዋል፡፡

  2. አቅራቢዎች የዞኑ ማረሚያ ቤት በሚገኝበት ከተማ (አሰላ ከተማ) ውስጥ ለምግብ እህል ከምችት የሚያገለግሉ መጋዘን ያላቸው ወይም የበሰሉ ምግቦችን ማዘጋጀት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 (ሰላሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በዞኑ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት የግዢ ዕቅድና አስተ/ፋይናንስ ድጋፍ ሰጪ የስራ ሂደት ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

  4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በዝግ ፖስታ በማድረግ በአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡

  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያን ከመቶ ሁለት (2 ፐርሰንት) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ብቻ እና የእህሉን ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  6. በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የሚቀርቡ ማህበራት ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል፡፡

  7. ጨረታው የሚከፈተው ሐምሌ 20 ቀን 2008 ዓ.ም ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ በ5፡00 ሰዓት አርሲ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎችና የመ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል፡፡

  8. ማ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ውሉን የመሰረዝም ሆነ ሙሉ በሙሉ የማቋረጭ መብት አለው፡፡

  9. ተጫራቾች የምግብ እህሉንም ሆነ ማጣፈጫዎችን እና የማገዶ እንጨት በራሳቸው መጓጓዣ ወጭ እስከ ማረሚያ ቤት ድረስ ማቅረብ ወይም የበሰለ ምግብ ማዘጋጀት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  10. 10.  ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 022331040/0922651585 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡