Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአቡና ግንደበረት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-08-23

 

Tender Detail:

 

 

በምዕራብ ሸዋ ዞን የአቡና ግንደበረት ወረዳ የገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉት ለመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች (Electronics, Furniture & relating materials)፣ የጽዳት መሳሪያዎችና የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና ከጉዳዩ ጋር በቀጥታ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡

  2. የዘመኑን የሥራ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፡፡

  3. ተጫራቹ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ያለውና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡

  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ከምያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ቢድ ቦንድ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ (CPO)  ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ የምትችሉ ሆኖ በመንግስት የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችም ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 12 /አስራ ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ከፍለው ከአቡና ግንደበረት ወረዳ የገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በስራ ሰዓት መውሰድ ይቻላል፡፡

  6. ተጫራቹ በውሉ መሰረት፣ የሚያቀርቡት ዕቃ ደረጃውን የጠበቀና በመስሪያ ቤቱ ቦታ ንብረት ክፍል ገቢ የሚያደርግ፡፡

  7. ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በመሙላት ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈር ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 16/12/2008 ዓ.ም ድረስ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  8. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 6፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በመስሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይሳተፉም የጨረታው መክፈቻ ይቀጥላል፡፡


  9. አሸናፊው ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ላሉት 5 (አምስት) የሥራ ቀናት በኃላ ቀርቦ ውል ካልፈጸመና ከጨረታ መውጣት ከፈለገ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው CPO ይወረስበታል፡፡

10.ጨረታው ከተከፈተ በኃላ የቀረበውን የመወዳደሪያ ሀሳብ መቀየር ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታው መውጣት አይቻልም፡፡

11.አሸናፊ ተጫራቾች ቅድመ ክፍያ የሚያገኙት ከሚያቀርቡት ዕቃ 50% ገቢ ካደረጉ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ 30% መጠየቅ ይችላሉ፡፡

12.ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካለበት ጨረታው ከተከፈተው ቀን አንስቶ ተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ 

13.ተጫራቹ ናሙና ማቅረብ የሚችልና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% (with holding) የሚቆርጡ 

14.ተጫራቾቹ የ2008 ግዥ ጨረታውን አሸንፎ ዕቃውን ሲያቀርቡ የወረዳውን ግዥ ያስተጓጎሉ ተጫራቾች መሳተፍ አይችሉም፡፡

15.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0910 12 15 70 /0913 11 28 81/0920 0417 65/
0116 56 63 00 /0921 53 96 86/ 0943 1318 43

የአቡና ግንደበረት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት