Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደር

Dead Line: 2016-08-21

 

Tender Detail:

 ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደር የግምብቹ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለ2009 በጀት ዓመት በወረዳ ስር ላሉት መስሪያ ቤቶች የደንብ ልብስና ጫማ፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሞተር ጎማ፣ ከመነዳሪና የተለያዩ የሞተር መለዋወጫ እቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ሼልፎችና መደርደሪያዎች፣ የቴክኒክና ሙያ የሚሆኑ ማሽኖችና ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

1. ለጠቀሱት ዕቃዎች ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና ማቅረብ የሚችሉ

3. በፌዴራል ወይም በክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዘጋቢ የሆኑ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡

4. የጨረታው ሰነድ የማይመለስ 250 /ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በምስራቅ ሸዋ ዞን በግምብቹ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ ከነዋጋው ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በጨረታውም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው የሥራ ቅን 5፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡20 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 1 የሚከፈት ይሆናል፡፡

6. ማንኛውም ተጫራች ከሚያቀርባቸው ጠቅላላ ዋጋ 20,000 /ሃያ ሺ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ በግምብቹ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7. አሸናፊ ተጫራች በራሱ መጓጓዥያ /ትራንስፖርት/ ንብረቶችን በምስራቅ ሸዋ ዞን ግንብቹ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ጨፌ ዶንሳ አምጥቶ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ በደብረዘይት 82 ኪ.ሜ ሲሆን በሰንዳፋ 65 ኪ.ሜ ላይ ነች፡፡


ለተጨማሪ ማስረጃ፡- 0224510008/0920949420
በምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳድር የጊምብቹ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት