Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Dead Line: 2016-08-21

 

Tender Detail:

 




በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ (ኢትፍሩት) ለሽያጭ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የፋብሪካ ውጤቶችን

1ኛ. ፓስታ፣ 2ኛ. መኮሮኒ፣ 3ኛ. የስንዴ ዱቄት፣ 4ኛ. ከአኩሪ አተር የተዘጋጀ የምግብ ዘይት፣ 5ኛ. ከለውዝ /አቾሎኒ የተዘጋጀ የምግብ ዘይት፣ 6ኛ. ከኑግ ዘር የተዘጋጀ የምግብ ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉበት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆን አለባቸው፡፡

  2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የምርት ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫና ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  3. በጨረታው ሰነድ ላይ በሎት ቁጥር ተከፋፍሎ በዝርዝር የተገለጹትን ምርቶች የማቅረቢያ ጊዜ በውል ስምምነት የሚገለጽ ሆኖ አሸናፊው ተጫራች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባሉት የግዥ መጋዘኖች በራሱ ትራንስፖርት አቅርቦት ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

  4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኃላ ከ7፡00-10፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ከንግድ ዘርፉ የፋይናንስና ንብረት አቅርቦት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ፡፡

  5. ተጫራቾች የምርቱን ነጠላ ዋጋ ከቫት ጋር የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በማዘጋጀትና በመሙላት ስልጣን በተሰጠው አካል በማስፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በንግድ ዘርፉ የግዥና ሽያጭ ወሳኝ የሥራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 13 ቀን 2008 ዓ.ም በጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ነሐሴ 17 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ነሐሴ 17 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጨረታ የሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ በየሎት ቁጥር 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

  7. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች ተፈላጊ ሰነዶችን ለየብቻው በአንድ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  8. ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለውና በግልጽ የሚነበብ መሆን ይኖርበታል፡፡

10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ራሳቸውን ከጨረታ ማግለል የማይችሉ ሲሆን ካገለሉ የጨረታ ማስከበሪያው ተይዞ ለንግድ ዘርፉ ገቢ ይሆናል፡፡

11. አሸናፊው ማሸነፉ እንደተገለፀለት በ5 ቀን ውስጥ ቀርቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል በመዋዋል ምርቶችን ማቅረብ አለበት፡፡

12. የንግድ ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. ጨረታ የሚካሄድበት አድራሻ ቦታ፡- በንግድ ዘርፉ ዋና መ/ቤት ቄራ በሚገኘው ቅጥር ግቢ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

በስልክ ቁጥር 0911 47 99 41/ 0911 68 26 71/0114166100፣

ፋክስ ቁጥር 0114 163631

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን