Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ

Dead Line: 2016-02-24

 

Tender Detail:

 

 የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት የሥራ ሂደት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለማስታወቂያ አገልግሎት የሚውል ኤልኢዲ እና ለስጦታ አገልግሎት የሚውሉ የቆዳ ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ለጨረታ ቁጥር ቢዴ/02/2016 

የሥራው ዓይነት

ካቢኔት መጠን

ብዛት

የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይንም ቅድመ ሁኔታ ባስቀመጠው የባንክ ዋስትና(ብር)

ማስታወቂያዎችን በጽሁፍ ምልክት፤በድምጽ እና በቪዲዩ የተቀረጹ ምስሎችን የሚያስተላልፍ ባለሙሉ ቀለም ኤልኢዲ ዲስፕሌይ
( full color LED display) በማቅረብ በተጠቀሰው የባንክ ቅርንጫፎች የመስቀል ስራ

120 cm * 180 cm

200

100,000.00

   በጨረታው ለማካፈል የምትፈልጉ ሁሉ

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን፤በመንግስት ግዥና አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ውስጥ የተመዘገቡበትን፤የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበቡበትን ማስረጃ ሠርተፍኬት ማቅረብ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ ለእያንዳንዱ የጨረታ  ሰነድ የማይመለስ ብር 110/መቶ አንድ ብር/በኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ስላሴ ቅርንጫፍ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከረቡዕ የካቲት 2 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ዘውትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00-10፡30 ሰዓት ቅደስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ ላይ በሚገኘው የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 208 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ስለ ጨረታው መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-122-89-66 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  3. ለጨረታ ቁጥር ቢዴ/02/2016 ጨረታ የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከላይ ከተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው ቦታ ይዘጋል ፡፡ተጫራቾች እስከ የካቲት 17 ቀን 200 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እያስመዘገቡ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለጨረታ ቁጥር ቢዴ/02/2016 ጨረታ የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ከላይ ከተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው ቦታ ለመገኘት ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው የፍላገት መግለጫ ዝርዝር መሰረት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡