Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: በአብከመ ደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ወረኢሉ ወረዳ ቅ/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-10-24

 

Tender Detail:

 



በአብከመ ደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ወረኢሉ ወረዳ ቅ/ጽ/ቤት ለሚያስገነባው በአለም ባንክ በጀት ብሩህ ተስፋ ት/ቤት ሙሉ ማቴሪያሎች ግንባታና የወ/ወ/ውሃና ኢነርጂ ጽ/ቤት የቆርቆሮ በቆርቆሮ ቤት ግንባታ በወረዳ ካፒታል በጀት የስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት የስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ለዚህም የስራ ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው፡-

1.በግንባታ ሙያዎች ወይንም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 9GC በላይ የስራ ፍቃድ ያለው፡፡

2.የታደሰ የሙያ ብቃት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፡፡

3.ህጋዊ የግንባታ ስራ ፈቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡

4.ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የድርጅቱን ስም የሚገልጽ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡

5.የፋብሪካ እና የአካባቢ ማቴሪያል ችሎ ሙሉ ስራውን መስራት የሚችል (ለት/ት ጽ/ቤት ግንባታ)

6.የግንባታውን እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7.የግብር ከፋይ ምዝገባ ቲን ነምበር ያላቸው፡፡

8.ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም መኖር አለበት፡፡

9.በተቋራጩ (ጨረታ አሸናፊው) ችግር ስራው ቢጓተት /ቢበላሽ/ ከተሰጠው ዲዛይን ውጭ መስራቱ በባለሙያ ከተረጋገጠ ለባከነው የአካባቢም ሆነ የፋብሪካ ማቴሪያል ኪሳራው በራሱ ሆኖ ጽ/ቤቱ ስራውን አስቁሞ ውለታውን አቋርጦ የተሻለ አማራጭ ይጠቀማል፡፡

10.  ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያለተመሰረተ የባንክ ዋስትና 2% /ሁለት ፐርሰንት/ በመግዛት መሙላት አለበት፡፡

11.  በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በመሙላት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት መሙላት አለበት፡፡

12.  ከላይ በተዘረዘረው መሰረት የምታሟሉ ተጫራቾ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለተከታታይ 30 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡
ጨረታውም በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት ጨረታው በይፋ ይከፈታል፡፡

13.  ተጫራቾ በጨረታው ሰዓት በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው የሚከፈትበትን ሰዓት ላይ የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከሆነ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል፡፡


14.  የጨረታ ማሸጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

15.  ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 033 116 01 99/54 መደወል ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡