Tenders

 

Type: Machinary

 

Organization: የደ/ብ/ብሕ/ክ/መ/ትምህርት ቢሮ

Dead Line: 2016-10-08

 

Tender Detail:

 




የደ/ብ/ብሕ/ክ/መ/ትምህርት ቢሮ
 ለየ2009 ዓ.ም ዓመታዊ 1 ጄኔሬተር ግዥና ተከላ በስራ መስኩ የተሰማሩትን የንግድ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና ተጨማሪ እሴት ታክስ የከፈሉበትንና የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፣ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ፣ መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

  2. የንግድ ፈቃዳቸውንና የምዝገባ ሰርተፊኬታቸውን የዘመኑን ያሳደሱ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ትምህርት ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ለስራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የአንዱን ዋጋ ሞልተው ኦርጅናል እና ኮፒ ለይቶ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮ ቁጥር 102 ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 1% የጨረታ ዋስትና (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

  6. መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0462 20 9637 መጠየቅ ይችላሉ፡፡