Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Dead Line: 2016-10-08

 

Tender Detail:

 



የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ያገለገሉ የተለያዩ መኪናዎችን ጀነሬተሮች ዲናሞዎች ሞተር ሳይክሎችን እና የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች ዝርዝር የመጫረቻ ሰነድ ጋዜጣው ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ እስከ 15 ባሉት ቀናት ለመኪና ብር 200 ብር ለሞተር ሳይክሎች 100 ብር ለጀነሬተሮችና ለዲናሞዎች ብር 100 እና ለብረታ ብረቶች ብር 100 በመክፈል ከአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃዎች መነሻ የጨረታ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 30% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 

3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ/ በማሸግ ለስራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ በአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡

4ኛ. ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ጨረታው ሂደት እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡

5ኛ. ማንኛውም ተጫራች ተጫርቶ ያሸነፋቸውን ንብረት ካሸነፈበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን ፈጽሞ የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡ ንብረቱን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ክፍያውን አጠናቆ የማያነሳ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ እንደገና ንብረቱ ለጨረታ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

6. ለተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ለመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ሲሆን ከስም ማዛወር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በገዥው የሚሸፈን ይሆናል፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ካስያዘው ንብረት ውጭ መወዳደር አይችልም፡፡

8. ምንም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ/አማራጭ/ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0468810369/0468812049/መደወል ይቻላል፡፡

 በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጋሞ ጎፋ ዞን የአርባ ምንጭ ከተማ ውሃ እናፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት