Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር

Dead Line: 2016-10-11

 

Tender Detail:

 የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለ2009 በጀት ዓመት የቶምቦላ ሎተሪ ሽልማት የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መኖሪያ ቤቶች ተሽከርካሪ መኪናዎችን ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 1. መኖሪያ ቤት ባለ አንድ ፎቅ (G+1 ) ……………………ብዛት 1

 2. መኖሪያ ቤት ባለ ሶስት መኝታ ቪላ………………….ብዛት 1

 3. መኖሪያ ቤት ባለ ሁለት መኝታ ቪላ…………………ብዛት 1

 4. 60 ሰው የሚጭን የህዝብ ማመላለሻ……………………ብዛት 1

 5. የቤት አውቶሞቢሎች የተለያዩ ሲሲ ያላቸው……………………ብዛት 5

 6. ሞተር ብስክሌት 150 ሲሲ……………………ብዛት 5

 7. ቴሌቭዥን 43 ኢንች/ LCD/……………………ብዛት 6

 8. ላፕቶፕ ኮምፒውተር……………………ብዛት 50

 9. የልብስ ማጠቢያ ማሽን 16 ኪሎ……………………ብዛት 50

 10.  ማቀዝቀዣ 200- 240 ሊትር/2 በር ያለው/……………………ብዛት51

 11. በኤሌክትሪክና በጋዝ የሚሰራ ምድጃ……………………ብዛት 50

 12. የውኃ ማጣሪያ 20 ሊትር ከነማቀዝቀዣው ……………………ብዛት 50

 13. የሞባየል ቀፎ……………………ብዛት 500

 14. ዲጂታል ካሜራ ……………………ብዛት 500

 15. የቡና ማፍያ በኤሌክትሪክ የሚሰራ……………………ብዛት 500

 16. አንደኛ ደረጃ የሳሎን ሶፋ ከነጠረጴዛው……………………ብዛት 1

 17. አንደኛ ደረጃ ባለ 1.50ሜ አልጋ ከነፍራሹ ……………………ብዛት 1

 18. አንደኛ ደረጃ የሳሎን ኮንትሮል ቡፌ……………………ብዛት 1

ለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ  በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጥቅምት  1 ቀን 2009 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን  ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈልና በመግዛት  መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ  ፈቃዳቸውንና  ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10፣000 በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ አድርገው ደረሰኙን ማያያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች  የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና የጨረታ ማስከበሪያውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2009 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 1ቀን 2009 ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ አስተዳደሩ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 011-1-56-90-65 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡