Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶሊበን ወረዳ የገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-10-08

 

Tender Detail:

 

 


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶሊበን ወረዳ የገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የ2009 ዓ.ም የሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን አቅርቦቶችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የህንጻ መሳሪያ፣ ሎት 4 የውጭ ስሪት ፈርኒቸር፣ ሎት 5 የአገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 6 የጽዳት እቃ፣ ሎት 7 የተሰፉ የደንብ ልብስ፣ ሎት 8 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት 9 ጫማ፣ ሎት 10 አሸዋ፣ ሎት 11 ሲሚንቶ፣ ሎት 12 የመኪና እቃ፣ ሎት 13 የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና ሎት 14 የስፖርት ትጥቅ ሲሆን በዚህም መሰረት፡-

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡

  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡    

  4. የግዥ መጠኑ ከ50,000 (ከሃምሳ ሺ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ VAT የከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

  5. ተጫራቾ በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡

  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1.500 ብር፣ ለሎት 2. 500 ብር፣ ለሎት 3. 500 ብር፣ ለሎት 4. 500 ብር፣ ለሎት 5. 300 ብር ለሎት 6. 300 ብር፣ ለሎት 7. 300 ብር፣ ለሎት 8 300 ብር፣ ለሎት 9 300 ብር፣ ለሎት 10 300 ብር ለሎት 11 300 ብር፣ ለሎት 12 500 ብር፣ ለሎት 13 300 ብር እና ሎት 14 300 ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ በማሸግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለባሶ ሊበን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-11፡30 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9.ይህ ግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ ይውላል፡፡


10.  ለሎት 12 የመኪና እቃ ኦርጂናል እቃ መሆኑን በውል በያዝነው የጥገና ጋራዥ ተረጋግጦ የሚገባ ይሆናል፡፡


11.  ይህ ግልጽ ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በእዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ/ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 14 በግልጽ ይከፈታል፡፡ በዓል ከሆነ በተከታታይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡


12.  መሰረዝ መደለዝ አይቻልም ስርዝ ድልዝ ቢኖረውም እንኳ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡


13.  ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ለመክፈት የማያግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡


14.  ጨረታው በሎት ወይም በድምር ስለሆነ ተጫራቾች ሁሉንም መሙላት አለባቸው፡፡


15.  አሸናፊው አካል ውጤቱ ከተነገረው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሞላው ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡


16.  አሸናፊው የአሸነፈበትን እቃ ኦርጅናል እቃዎችን ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡


17.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0582460316 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡