Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

Dead Line: 2016-10-14

 

Tender Detail:

 




የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በበጀት አመቱ የሚያሰራጨውን የደንብ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የዕቃዎች ዝርዝር

መለኪያ

ብዛት

1

ብትን ጨርቅ አንደኛ ደረጃ ቴትሮን 6000 ቀለም ጥቁር ሰማያዊ

ሜትር

924.64

2

ብትን ጨርቅ አንደኛ ደረጃ ቴትሮን 6000 ቀለም ጥቁር የጨርቁ ጥራትና ቀለም በተጠቃሚዎች የሚመረጥ

ሜትር

960.60

3

የውስጥ ልብስ ብትን ጨርቅ

ሜትር

657

4

ሻሽ

ቁጥር

96

5

የተለያዩ መጠን ያለው የወንድ ሸሚዝ

ቁጥር

888

6

ቆዳ ጉርድ ጫማ የወንድ

ጥንድ

448

7

ቆዳ  ጉርድ ጫማ የሴት

ጥንድ

154

8

ከረቫት

ቁጥር

440

9

ካልሲ

ቁጥር

920

10

ገበር ያለው የዝናብ ልብስ

ቁጥር

243

11

ጋዋን (ጥቁር ሰማያዊ)

ቁጥር

170

12

ጋዋን(ነጭ)

ቁጥር

102

13

 ዣንጥላ የወንድ

ቁጥር

20

14

ዣንጥላ የሴት

ቁጥር

60

15

 ቡትስ ቆዳ ጫማ

ጥንድ

7

16

ሴፍቲ ጫማ

ጥንድ

140

17

በአንደኛ ደረጃ ቴትረን 6000 ጨርቅ የተሰፋ ሜንዞ (ኮትና ሱሪ ያለው) ቱታ

ቁጥር

100

18

ፖል ቲሸርት

ቁጥር

50

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስረዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ ገጽ (Website)  አትመው ከጨረታው ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸወዋል፡፡

  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)   ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

  3. ተጫራቾች አንድ ወይም ሁለት ዓይነት የደንብ ልብስ ለመጫረት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10.000 /አስር ሺህ ብር/ እንዲሁም ከሁለት ዓይነት በላይ የደንብ አልባሳት ለመጫረት የሚፈልጉ ብር 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ  የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን  ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

  5. ተጫራቶች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሰዓት እና ከምሳ ሰዓት በኋላ 7፡30 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋሲሊቲ ማኔጅመንት የስብሰባ አዳራሽ በዕለቱ ማለትም ጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  7. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-5512400 የውስጥ መስመር 217 ወይም በቀጥታ 011-550 49 31 መጠየቅ ይችላሉ፡፡