Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: ደራ ትሬዲንግ አክስዮን ማህበር

Dead Line: 2016-10-12

 

Tender Detail:

 





ደራ ትሬዲንግ አክስዮን ማህበር
የ2009/2010 ስሪት የሆኑትና የመጫን አቅማቸው400 ኩንታል የሆነ ሃይቤድ ሲኖ ትራክ የጭነት መኪኖች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ
አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይምድርጅት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይቻላል፡፡
 
1.ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበትቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል
የጨረታ ሰነዱን ደንበል ሲቲ ሴንተር 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 914 በግንባር ቀርበውመግዛት ይችላሉ፡፡


 
2.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከገዛ በኋላ ተሸከርካሪዎቹ በሚገኙበትቃሊቲ ወርቁ ሰፈር በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ጠጠር ማምረቻ ግቢ
ውስጥ በመገኘት መኪኖቹን ማየት ይችላል፡፡


3.ማንኛውም ተጫራች ለያንዳንዱ መኪና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ)ለአንድ መኪና የሚሰጠው ዋጋ 10% በባንክ ሰርቲፋይድ በሆነ ቼክ (CPO) ከዋጋ
ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡


4.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ለዚሁ ጨረታበተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከታች በተገለጸው አድራሻ ቀርበው ማስገባት ይችላሉ፡፡

 
5.ዝግ ጨረታው ጥቅምት 1 ቀን ከቀኑ በ10 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ማለትም ጥቅምት 2 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ
ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6.ማንኛውም ተጫራች ለአንድ መኪና በሚያቀርበው ዋጋ ላይ ከነተጨማሪ እሴትታክስ 15% ጋር መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ አለበት፡፡

 
7.ማንኛውም ተጫራች ለአንድ ወይም ለሁሉም መኪኖች መወዳደር ይችላል፡፡

ይሁን አንጂ ዋና መኪና (ጎታች) እና ተሳቢ ነጣጥሎ መወዳደር አይቻልም፡፡

መወዳደር የሚቻለው መኪናው ከነተሳቢው አንድ ላይ ዋጋ በመስጠት ነው፡፡


8.አሸናፊ ተጫራች ጨረታ ማሸነፉን ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ ፈጽሞ መኪኖቹን ማንሳት አለበት፡፡ አሸናፊዎች
ያሸነፉበትን ዋጋ ከፍለው ካላነሱ ያስያዙት 10% CPO (ገንዘብ) ለድርጅቱ ገቢይሆናል፡፡


9.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝመብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 
10.አድራሻ፡- ደራ ትሬዲንግ አክስዮን ማህበር ደምበል ሲቲ ሴንተር 9ኛ ፎቅ
ቢሮ ቁጥር 914 ስ.ቁ. 0115528706/07 ሞባይል፡ 0930099960 አዲስ አበባ