Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በስኳር ኮርፖሬሽን መተሐራ ስኳር ፋብሪካ

Dead Line: 2016-10-17

 

Tender Detail:

 





በስኳር ኮርፖሬሽን መተሐራ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ ለፋብሪካው አገልግሎት የሚውሉ ጥራታቸውን የጠበቁ ዕቃዎችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው ጥቅል መሰረት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ጥቅል 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች (stationery items)

ጥቅል 2. የቆዳ የእጅ ጓንት (Leather gloves)

ጥቅል 3. የሰሌን ኮፊያ (Straw Hat), የዘንባባ መጥረጊያ (Zambaba Brooms), እና የጽዳት መጠበቂያ ዕቃዎች (Bleech & OMO)

ጥቅል 4. የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች (Vehicle Battries)

ጥቅል 6. ኮስቲክ ሶዳ ኬሚካልስ (caustic soda in flask 98%)

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡  

  1. ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል ጨረታ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፊኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ጨረታ ለተወዳደሩበት ዓይነት የጠቅላላ ዋጋውን ቢያንስ 2% በሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እ.ኢት.አ. ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 0115 50 56 07/0115 50 58 21 ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ አዲስ አበባ

 በስኳር ኮርፖሬሽን የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ግዥ ቡድን