Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን የደ/ብ/ከ/ለኢንዱስትሪ ሼድ ግንባታ ፕሮጅክት

Dead Line: 2016-10-16

 

Tender Detail:

 

 


በአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን የደ/ብ/ከ/ለኢንዱስትሪ ሼድ ግንባታ ፕሮጅክት ለሼድ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የግንባታ ዕቃ ለመግዛት እና የተለያዩ የግንባታ ተረፈ ምርት ለመሸጥ የስራው ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዟል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈረቶች በማሟላት መጫረት ይችላሉ፡፡

ሎት 1 የአካባቢ የግንባታ ግብአት ግዢ (ጠጠር፣ ገረጋንቲ፣ ቀይ አፈር፣ ፑሚስ፣ አሸዋ፣ እንጨት በር…)

ሎት 2 የግንባታ ኬሚካል ግዢ (expoxy, filant, water proof admixture …)

ሎት 3 ልዩ ልዩ የፋብሪካ እቃዎች ግዢ (ሳኒቴሪ እቃ፣ 6 ሚ/ሜ መስታዎት፣የኮንክሪት አስፋልት፣ የእጅ መሳሪያ፣LTZ፣አንግል አይረን፣ 0.8 ሚ/ሜ ልሙጥና ሀዲድ ላሜራ)

ሎት 4 ሲሚንቶ OPC ግዢ (ደርባ፣ ዳንጎቴ፣ ሙገር፣ መሶቦ …)

ሎት 5 ማሽነሪ ኪራይ (ኤክስካቫተር ከነጃካቨሩ፣ 16ቶን ሮሎ፣ ግሬደር፣ ሻወርትሪክ …)

ሎተ 6 የማሽነሪ ጥገና (ሰርቪስ መኪና፣ ሚክሰር፣ ኮምፓክተር፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች…)

ሎት 7 የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች ግዢ (የሳኒተሪ እቃ፣ ሻወር ቤት እቃ …)

ሎት 8 የጣሪያ እቃ ግዢ (ሞራሌ፣ ኮርነር ሊስት…)

ሎት 9 ልዩ ልዩ የግንባታ ተረፈ ምርት በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ዝርዝሩ በስፔስፊኬሽኑ ላይ ተገልጻል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ የጨረታ ሰነዱን ደብረ ብርሃን ከተማ ዳሽን ቢራ አጠገብ በሚገኘው ሼድ ግንባታ ፕ/ጽ/ቤት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 10.00 /አስር ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡ እቃውን ዝርዝር በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ የሚገለፅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለመጫረት የሚያስፈልጉ እና ማሟላት የሚገባቸው

  1. ተጫራቾች ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ በ9፡00 ሰዓት በፕ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡

  3. በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ መሟላት ያለበት፡፡

-    በዘርፍ የንግድ ስራ ፈቃድና ለዘመኑ ስለመታደሱ ማረጋገጫ፣

-    ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ገቢ ግብር ለመክፈላችሁ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣት ማረጋገጫ፣

-    የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /VAT/ Reg.certificate/፣

-    የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫት ጨምሮ ለእያንዳንዱ ሎት 5000 ብር/አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ይኖርበታል፡፡

-    ለማሽነሪ ኪራይ ተወዳዳሪዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

-    በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡

-    ከ50 ሺህ ብር በታች ለሚጠይቁ ግዢዎችና አገልግሎቶች TOT ተመዝጋቢ መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. የጨረታ አሸናፊው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና /ፐርፎርማንስ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡

  2. የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡

  3. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችሉም፡፡

  4. በጨረታ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገፅ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡

  5. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓተ ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

  6. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሰው

አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 011 8909055/011 8909051

 በአብክመ ኮንስትራክሽን ቤ/ልማት ኤጀንሲ የደ/ብ/ከ/ማ/ግ/ፕ/ጽ/ቤት ደ/ብርሃን