Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-10-14

 

Tender Detail:

 

 

 

 

በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የተለያዩ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ዕቃዎችና የተሰባበሩ ጋሪዎችና ደስትቢኖችና የተለያዩ ቁሳቁሶችን እንዲሁም አልባሳት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለጨረታው መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

  1. በጨረታው መወዳደር የሚችሉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000.00 ብር /ሁለት ሺ ብር/ በባንክ የተመሰረከረ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል
  3. የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ከጣይቱ ሆቴል ወረድ ብሎ በሚገኘው በፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10 የስራ ቀን በወረዳው ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ10ኛ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
  5. በዛው ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር 4ኛ ፎቅ አዳራሽ ፎቅ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ከጣይቱ ሆቴል ዝቅ ብሎ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ስልክ ቁጥር 011 111 22 87 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት