Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በምስራቅ ሐረርጌ የቁምቢ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-10-06

 

Tender Detail:

 





በምስራቅ ሐረርጌ ለቁምቢ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በስሩ ላሉት መስሪያ ቤቶች ለ2009 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚውል፣ የተለያዩ የጸሕፈት መሳሪያዎች /አላቂ ዕቃዎች/ የቋሚ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት ዕቃ፣ የተለያዩ ደረቅ ምግቦች፣ የሞተር ሳይክል ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት ስራ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ የሚያሟሉ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተጫራቾች የምትወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) የተረጋገጠ ባንክ (CPO) በጥሬ ገንዘብ ብር ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የግብር ከፋይነት ቁጥር (TIN) ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (ቫት) ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች ጨረታው ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ቁምቢ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ ማድረስ የሚችሉ፣
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበተ ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀናት በማይመለስ ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቁምቢ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል (ዝግ) ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀናት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ /አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በውል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ቢሮው 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  9. የበለጠ መረጃ ለማግኘት ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0920895072/0915093877/0921246303 ደውለው ወይም መስሪያ ቤታችን ድረስ በጽሑፍም ሆነ በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ፡፡

 በምስራቅ ሐረርጌ የቁምቢ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት