Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሐምሌ 19 ቁ. 2 የመ/ደ/ት/ቤት

Dead Line: 2016-10-15

 

Tender Detail:

 



በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሐምሌ 19 ቁ. 2 የመ/ደ/ት/ቤት በ2009 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የደንብ ልብስ፣

  2. የትምህርት መገልገያ ዕቃዎች፣

  3. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች/የጽህፈት ዕቃዎች፣

  4. የጽዳት ዕቃዎች እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣

  5. ህትመት፣

  6. የደንብ ልብስ ስፌት

ለመግዛት ስለምንፈልግ ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሀናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ) ብር በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐምሌ 19 ቀ.2 የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁ.2 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ብር 3000.00 (ሦስት ሺህ) ብር (በሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡

ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ዕቃ ዓይነት ናሙና የማቅረቢያው ጊዜ ጨረታው ሳይከፈት ሦስት ተከታታይ የስራ ቀናት ሲቀረው ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዕቃ ከነቫቱ የዋጋ ዝርዝር በሚገዛው ሰነድ ላይ ይገልፃል፡፡

ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ኮልፌ 18 ማዞሪያ ከደጉ ሆቴል ፊት ለፊት ወደ ውስጥ በሚያስገባው አስፓልት መንገድ 200 ሜ እንደተጓዙ

ስልክ ቁጥር 011 279 17 18

 ሐምሌ 19 ቁ.2 የመ/ደ/ት/ቤት