Catagory Lists
Tenders
Type: Construction
Organization: የባምባሴ ወረዳ አቅ/ግን/ትም/ጽ/ቤት የአፋ-ፌርበርናሬ እና የኢዳ-ዳቡስ ቀበሌ የትምህርት ቤት
Dead Line: 2016-10-28
Tender Detail:
የባምባሴ ወረዳ አቅ/ግን/ትም/ጽ/ቤት የአፋ-ፌርበርናሬ እና የኢዳ-ዳቡስ ቀበሌ የትምህርት ቤት ሙሉ ግንባታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታው መስፈርቶች፡-
- የሥራ ፈቃዳቸው ደረጃ G/C ወይም B/C 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የስራ ፈቃዳቸውን ያደሱ፣ እንዲሁም በክልሉ የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተቋራጮች የጨረታው ሰነድ ይን ማስታወቂያ ከወጣበትን ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከባምባሲ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሰነዱን 1 ኦሪጅናል እና 2 ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸግ ኢንቨሎፕና 3ቱንም በ1 በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቦንድ CPO ወይም ህጋዊ መድን ዋስትና የተረጋገጠ 2% ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ያላቸውን የሰው ኃይል ወይም ባሙያዎቻቸውን በክልሉ የብቃት ምዘና ምዝገባ ያደረጉ/ያላቸው ፋይናንስ ካፒታል /ገንዘብ ማሽነሪና ሊብሬአቸውን (Company profile) ማስረጃዎቻቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጨማሪ ማስረጃ ካስፈለገ ከጽ/ቤቱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበተ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ በባምባሲ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት እንደተገለጸ ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- በክልሉ የተደራጁ የሙያ ማህበራት ለዚሁ ስራ ብቻ ካደራጃቸው መ/ቤት የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 0917422582/0917171470 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀናት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ላይ በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
የቤ/ጉ/ክ/መ/አሶ/ዞን/ባምባሲ ወረዳ ገን/ኢ/ል/ጽ/ቤት