Tenders

 

Type: Laboratory Equipments & Chemic

 

Organization: የባቱ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Dead Line: 2016-10-21

 

Tender Detail:

 




ድርጅታችን ለከተማው መጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚውሉ፡-

1. የውሃ ማጣሪያ ኬሚካሎች

1.1 አልሙኒየም ሰልፌት

1.2 ክሎሪን (ፓውደር)

በመሆኑም ከታች የተጠቀሱት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የባቱ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመገኘት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች እያንዳንዱን እቃ የሚሸጡበትን ዋጋና ጠቅላላውን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻና የጨረታውን ዓይነት በመጥቀስ ባቱ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታውን ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 11 ቀን 2009 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ነው፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈተው በእለቱ ጥቅምት 11 ቀን 2009 ዓ.ም ከረፋዱ በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቢሮ ውስጥ ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊዎች ያሸነፉበትን እቃ እስከ ድርጅቱ ድረስ በማቅረብ እቃው ትክክለኛነቱ በባለሙያ ሲረጋገጥ ክፍያ የሚከፈለው መሆኑን የሚስማማ መሆን አለበት፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 441 2497/046 441 2094 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የባቱ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት