Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-10-21

 

Tender Detail:

 





በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለወራቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል የመኪናዎች ጎማ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  • በመስኩ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  • የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ፣
  • በመንግስት ግዢ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ፣
  • የጨረታ ዋስትና 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፣

ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ወራቤ ከተማ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 50 (ሀምሳ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ከተገለጸው መጠን አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች የተገለጸውን የዕቃው ዓይነት ኦርጅናል ካላቀረበ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን የዕቃ ዓይነት በተገባው ውል መሰረት ካላቀረቡ ሲፒኦ የማይመለስ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  • አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኃላ ወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በአካል ተገኝቶ ውል መግባት እንዳለብ እንገልፃለን፡፡
  • የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467710211 ይደውሉ፡፡

 

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የወራቤ ከተማ

አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት