Catagory Lists
Tenders
Type: Construction
Organization: በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የሀብሮ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
Dead Line: 2016-10-16
Tender Detail:
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የሀብሮ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 1. ከሉጎ እስከ ዳንሴ ያለውን መንገድ ኮረት ማስነጠፍ 2. ከመልካበሎ እስከ ከለቻ ያለውን መንገድ ካልቨረት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመንገዱ መስሪያ የሚያስፈልጉ ማሽኖችን 1. Grader production date 2010 & HP = 200 model 140H የሆነ ማሽን መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾቹ ሕጋዊ የስራ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የማሽኑን ኪራይ የሚመጥነውን ብር ማስያዝ (በባንክ የተረጋገጠ) ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) በጥሬ ብር ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ዕቃውን በጥራትና በተዋዋሉበት ጊዜ ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ዓመት በዓል (ከመንግስት የስራ ቀን ውጪ) ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ማሽኑን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ሳይቱ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ የቀረበው ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ነጋዴው በራሱ ወጪ ማሽኑን የመለወጥ ግዴታ አለበት፡፡ የማስጫኛና መውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ ብር አንድ መቶ (100) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ከሀብሮ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመንግስት ስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ተጫራቾቹ (ሕጋዊ ውክልና ያላቸው) በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መስሪያ ቤቱ የተለየ አማራጭ ካገኘ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ከሀብሮ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መረዳት ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር 0911 90 41 28/ 0255520009/105 ገለምሶ
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የሀብሮ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት