Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

Dead Line: 2016-10-22

 

Tender Detail:

 



ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁትን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1.የዕቃ አይነት፡- የጽህፈት መሳሪያዎች እና የቢሮ መገልገያ እቃዎች

ምርመራ፡- ጥቅል

2.የዕቃ አይነት፡- ህትመት

ምርመራ፡- ጥቅል 2

3.የዕቃ አይነት፡-የጽዳት እቃዎች

ምርመራ፡-ጥቅል 3

 ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ እና የታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ጎተራ ዋናው መ/ቤት ፋሲሊቲና ንብረት አስተዳደር መምሪያ (3ኛ ፎቅ) በመምጣት ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 50(ሃምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ/ጥቅል/ ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጥቅል ብር 10,000 በባንክ የተረጋገጠ ቼክ(ሲፒኦ) ከሚጫረቱበት ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የሚወዳደርበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨለፕ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ጥቅምት 14 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ (4ኛ ፎቅ) ይከፈታል፡፡

አንድ ተጫራች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይችልም፡፡

ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ናይል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት (ጎተራ)

ፋሲሊቲና ንብረት አስተዳደር መምሪያ (3ኛ ፎቅ)

የመ.ሳ.ቁ 12836

የስልክ ቁጥር፡- 011-442 60 00

አዲስ አበባ