Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ሴክተር በፖሊስ ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-10-28

 

Tender Detail:

 



የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ሴክተር በፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ የሙገቡ ቢሮዎች ግንባታ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ደረጃቸው  GC/BC-9 ብቻ የሆኑ ተጫራቾች በ2009 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

  2. ከክልሉ ወይም ከዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም መምሪያ የተመዘገቡና ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣

  3. የጨረታ ማስከበሪያ/Bid Bond/ የሚቀርበው ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍል ማዘዝ ወይም  CPO  ወይም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ የሚችሉ፣

  4. ተጫራቾች ህጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.እ.ታ /VAT   / የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ ብቻ ከይ/ዓለም ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍለው የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ከይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ሴክተር መውሰድ ይችላሉ፡፡

  5. ማንኛውም ተጫዋች ከውድድሩ በፊት የስራ ሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ ማረጋገጥ አለበት፡፡

  6. የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አራት ኮፒ ለየብቻቸው በሰም ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተከቶና በሁሉም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት እንዲሁም አድራሻ በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00-6፡00 ሰዓት ከይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ሴክተር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡

  8. አሰሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  9. ጨረታው ህጋዊ ሆኖ የሚቆየው/ የሚፀናው/ ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በ80 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡

የሲዳማ ዞን የይ/ዓለም ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት