Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Dead Line: 2016-11-07

 

Tender Detail:

 


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደደር ቅርንጫፍ የጥገና እና የማሻሻያሥራ ለማሰራት በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ በደረጃ 5 እናከዚያ በላይፍቃዳቸውንያሳደሱ፣ከመሠረተ ልማት ሚኒስቴር 
የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን አወዳድሮለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም

1.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የሥራ ተቋራጮችየተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር /በመክፈል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክፋሲሊቲዎች አስተዳደር በሚገኘበት ቫቲካን ኤምባሲ ወረድብሎ በቀድሞ ሚድሮክ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305ህንፃ ግንባታ ክፍል ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮመውሰድ ይችላሉ፡፡
 
2.ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒካል ሰነድ ዋናውንና አንድፎቶ ኮፒ እንዲሁም የዋጋ ሰነድ ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ(በማሽን ኮፒ) ሰነዶችን ለየብቻ የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስበሰም በታሸገ ኢንቭሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህአገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 07 ቀን 2009ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በፊት በማስመዝገብ ማስገባትአለባቸው።

3.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ (BID BOND) ብር25,000.00 / ሃያ አምስት ሺህ ብር /በባንክ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክዋስትና (unconditional Bank guarantee) ከጨረታ ሰነዱጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
 
4.ተጫራቾች ጨረታውን ሲገዙ የንግድ ፍቃድ፣ የሥራፍቃድ፣ የታክስ ከፋይነት ማስረጃ (ቲን ሰርተፍኬት) እናተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸውዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
 
5.ጨረታው ህዳር 07 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡30 ሰዓትተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር በሚገኝበት ቫቲካን ኤምባሲ ወረድ ብሎ በቀድሞ ሚድሮክ ህንፃ ላይበሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 
6.ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0113 – 20 45 88/72 28 72
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ