Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአዳማ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት

Dead Line: 2016-11-29

 

Tender Detail:

 



የአዳማ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ለአዳማ ከተማ 100ኛ ዓመት አከባበር አስመልክቶ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶችን በከተማዋ ላይ ማስዋቢያ የሚገኙ የውበት መገለጫዎችን ለማስዋብ መብራቶችና፡- ጌጣጌጦችን፡- በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች ባሉት የተጫራቾች መመሪያ በማንበብ ምወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡


2. ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (Vat) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡


3. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከአዳማ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡


4. ተጫራቾች የወዳደሩበትን የውድድር አይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ለጽ/ቤቱ በተሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ በነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋው ይወስዳል፡፡ በቁጥር በተጻፈው ዋጋ እና በፊደል በተጻፈው ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በፊደል የተጻፈው ይወስዳል፡፡

5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች ጽ/ቤታችን ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በከተማዋ መንገዶች ላይ የሚገኙ ለማስዋቢያ የውበት መገለጫዎችን ለማስዋብ መብራቶችና፡-
ጌጣጌጦችን፣ ሌሎችንም መስፈርቶች አይነት ሳይለወጥና ሳይነካካ በሰጠው እስፔስፊኬሽን ላይ በትክክል ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች በዚህ ስራ ላይ ማለትም በትልልቅ የከተማ በዓል ዝግጅት ላይ ከተማን የማስዋብ ስራ ልምድ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ስራዎችን በመስራት ልምድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

8. ለጨረታው የቀረበው ሰነድ ላይ አሞላሉ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ የሚታይ ሆኖ በአጋጣሚ ቢሳሳትና ቢስተካከል በቦታው ፎርማ ሊኖረው ይገባል፡፡

9. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍጹም አይቻልም፡፡

10. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ሲሆን፣ ሰነዱን በመግዛት በማንኛውም የስራ ሰዓት ሰነዱን ሞልቶ ከጨረሱ በትክክል በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ጠዋት 2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡


11. ጨረታው ጥቅምት 21/2009 ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም፡፡

12. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) በባንክ ቼክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

13. ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ላይ ቅሬታ ካለው በኦሮሚያ የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 157/2002 በቁጥር 61 ኣና 62 ባለው መሰረት በማመልከቻ ማቅረብ ይቻላል፡፡

14. መስሪያ ቤቱ የከተማዋን መንገድ ለማስዋብ የሚሰራባቸውን መንገዶች በኪሎ ሜትር በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው ርዝመቱ እንዳስፈላጊነቱ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ አዳማ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-811-94-83/0221-11-58- 63 ማነጋገር ይችላሉ፡፡