Tenders

 

Type: services

 

Organization: በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ

Dead Line: 2016-02-27

 

Tender Detail:

 

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ ግብይትና ኅብረት ሥራ ጽ/ቤት በወረዳችን ውስጥ ለሚገኙ ቀበሌያት በ2008 ዓ.ም ምርት ዘመን ለበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ ከመሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር መጋዘኖች ወደ የቀበሌያቶች እንዲጓጓላቸው የደረቅ ጭነት መኪና ለመከራየት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያለውና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለበት፤ስርዝ ድልዝ የሌለበት፤ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፡፡ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 100 ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ከወረዳው ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል/ፋይ/ንብ/አስ/ር ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO /ሲፒኦ / በካሽ / ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በሁምቦ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ክፍያ ንብ/አስ/ር ሥራ ሂደት አድራሻ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ኢንቨሎፕ መጨመር ይችላሉ፡፡ጨረታው ልክ ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
ዕለቱ ሰንበት ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡-0916457554/0928690938 ይደውሉ፡፡