Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የሲዳማ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ

Dead Line: 2016-11-14

 

Tender Detail:

 



የሲዳማ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በ2009 በጀት ዓመት በግቢው ውስጥ ያሉትን ህንጻ ቀለም ለማስቀባት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-

  1. ደረጃቸው GC-/BC-7  ከዚህያም በላይ የሆኑ ተጫራቾች በ2008/2009 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመሰረተ ልማት ሚ/ር የተመዘገቡና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣

  2. በማንኛውም ቦታ በግንባታ  ሂደት ችግር ምክኒያት ማስጠንቀቂያ ያልደረሰው ተቋራጭ የሆኑ፣

  3. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችና መሳሪያዎች በግላቸው አጓጉዘው ለሚሰሩ፣

  4. የጨረታ ማስከበሪያ( Bid Bond )  ከሚቀርበው የጠቅላላ ዋጋ 50000 (ሃምሳ ሺህ)  ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ፣


  5. ተጫራቾች ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.እ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ  ብር) በሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ከፍለው የከፈሉበትን ሰነድ በመያዝ ሲዳማ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡

  6. ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ በፊት የስራ ሳይት በራሱ ወጪ አይቶ ማረጋገጥ አለበት፣


  7. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ቢድ ቦንድ ኦርጅናሉና ሁለት ፎቶ ኮፒዎችን ለየብቻቸው በሰም ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ  ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ሕጋዊ የሆነ ማህተም  በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲዳማ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡


  8. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃዳቸውንና በመሰረተ ልማት የተመዘገቡበትን ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሰርተፍኬት አብሮ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡


  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣


  10. የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፣  የቀረበም የዋጋ የትንታን  መያያዝ አለበት፡፡


  11. አሸናፊው ተጫራች ከባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፣


  12. አሰሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፣

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው  የስራ ቀን ይሆናል፡፡