Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በጉለሌ ክ/ከተማ የአዲስ ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት

Dead Line: 2016-11-08

 

Tender Detail:

 




በጉለሌ ክ/ከተማ የአዲስ ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት በ2009 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ  ዕቃዎችን በሎት ከፋፍሎ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎች በሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች በሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች በሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃና የስፖርት ዕቃዎች በሎት 5 መጻሕፍት በሎት በዘርፉ ሕጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን በጨረታ  አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከታች የተገለጹትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በሚወዳደሩበት የሎት አይነት ተዛማጅ የሆኑ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የቲን ሰርተፍኬት የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ግብር የከፈሉበትን ጨረታ ለመሳተፍ  የተፈቀደበትንና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ስክሪን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 50 /ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ሽሮሜዳ በሚገኘው የት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመምጣት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡


  3. ተጫራቾች 2% የጨረታ ማስከበሪያ ከሰነዳቸው  ጋር አያይዘው እንዲሁም ካሸነፉ በኋላ 10% የውል ማስከበሪያ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች በት/ቤት ስም የተጻፈ የዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡


  4. ተጫራቾች ለጨረታው በተዘጋጀለት ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዳቸውን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡


  5. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡


  6. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል  የመሰረዝ  መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-  ሽሮሜዳ 31 ቁጥር ማዞሪያ ወደ ኪዳነምህረት በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ 50 ሜትር ገባ ብሎ፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡- 0111260995