Catagory Lists
Tenders
Type: Furniture
Organization: የእንሰሳትና አሳ ሀብት ሚ/ር
Dead Line: 2016-10-31
Tender Detail:
የእንሰሳትና አሳ ሀብት ሚ/ር ብዛት 71/ሰባ አንድ/መጠኑ 1.20* 1.20 የሆነ ባለ አራት ስቴሽን ጠረጴዛ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች ከተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ በተያያዘ ስለተሰማሩበት የስራ ዘርፍ በሚመለከተው አካል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
- ተጫራቾች ለተዘጋጀው ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በእንሰሳትና ዓሳ ሀብት ሚ/ር በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይቻላሉ፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 28 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚ/ር ሲ ብሎክ ላይ በሚገኘው ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከመገናኛ አለፍ ብሎ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ በማዕድን ሚ/ር ዝቅ ብሎ ቀድሞ ግብርና ሚ/ር ቅጽር ግቢ ውስጥ ሲ ብሎክ