Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: የሐበሻ ስሚንቶ አ.ማ

Dead Line: 2016-11-26

 

Tender Detail:

 



የሐበሻ ስሚንቶ አ.ማ ለፋብሪካው በአዲስ አበባ እና አካባቢው የሚገኙትን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ የትራንስፖርት ማህበራትን፣ የጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን ወይም ህጋዊ ግለሰብ ባለሃብቶችን በጨረታ አወዳድሮ ሊያሰራ ይፈልጋል::
 
1.ተጨራቶች በጨረታለመሳተፍ የሚያስችላችውን የዘመኑግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር ተዛመጅ የሆነ የንግድ ስራ ፍቃድ በማቅረብ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ቢጋር ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን እና በሪፖርትር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ) በመክፈል ወሎ ሰፈር ወንገላዊት ህንፃ ፊት ለፊት ካሳ ህንፃ 8ተኛፎቅ በሚገኘው የአክስዮን ማህበሩ ዋና መሰርያ ቤት በመቀረብ ከጥቅምት 23 ቀን 2009ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ::
 
2.በጨረታው አሸናፊየሚሆነው ተጫራች በቢጋር ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለሁሉም ተጫራቶች ክፍት ነው ::


3.በጨረታው አሸናፊ የሚሆን ድርጅት የተሸከርካሪው እስፖንዳ ለስሚንቶ ከረጢት መጫኛነት በሚመች ሁኔታ የተዘጋጀ ሆኖ 400ኩንታል እና ከዛ በላይ የመጫን አቅም ያላቸው፤ ይዞታቸው በጥሩ ሁኔታ ለይ የሚገኙ ፤ አክሲዮን ማህበሩ እንዲቀርብለት የሚፈልገውን የተሸከርካሪ ብዛት ጥያቄ ባቀረበ ጊዜ ተሸከርካሪውን ከአሽከርካሪው ጋር በወቅቱ እና በሰዓቱ ማቅረብ ይኖርበታል::
 
 
4.ተጫራቹ ለሚያቀርበው ተሸከርካሪ እና ለሚጭነው ጭነት ሙሉ የመድን ሽፋን እንዲሁም የሶስተኛ ወገን ዋስትና ማቅረብ አለባቸው::


5.አሸናፊው ተጫራች የሚያጓጉዘውን ሲሚንቶ መጠን እና የሚጓጓዝበትን ቦታ የሚወስነው አክሲዮን ማህበሩ ብቻ ነው::

 
6.ተጫራቶች የሚቀርበው ተሸከርካሪ የባለንብረቱ ለመሆኑ ሊብሬ እና ሌሎች የባለ ይዞታነት ማረጋጋጫ መቅረብ ይኖርባቸዋል:: አጓጓዡ የደረቅ ጭነት ባለንበረቶች ማህበር ከሆነ የሚያሰማራቸው መኪኖችየማህበሩ አባል ንብረት ለመሆናቸው ማረጋገጫ ሊያቀርብ ይገባል::

 
7.ተጫራቶች ጨረታሰነዳቸው በስም በታሸገ ኢንቮሎፕ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ እስከ ህዳር 17 ቀን 2009ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ስዓት ድረስ ማስገባት ይቻላሉ::
 
8.ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 17 ቀን 2009ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡ 30 ሰዓት ከታች በተጠቀሰው አድራሻ 8ተኛ ፎቅ በሚገኘው የአክስዮን ማህበሩ የመሰብሰብያ አዳራሽይከፈታል::

 
9.ተጫራቶች ሰነዳቸው ለጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በተዘጋጀው ቢጋር መሠረት በትክክል አዘጋጅተው ማቅረብ አለባቸው::ከቢጋሩ ደንብ እና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታተቀባይነት የለውም::

 
10.አክስዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 
11.ለበለጠ መረጃ ተጫራቶች የሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ::
ሐበሻ ሲሚንቶ አክስዮን ማህበር ኢትዮ ቻይና ፍሬንድሽፕ መንገድ(ዎሎሰፈር)   
ወንገላዊት ህንጻ ፊት ለፊት በሚገኘው ካሳ ህንፃ 8ተኛ ፎቅ
 
ስልክ ቁጥር 0114163273
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማሀበር