Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.)

Dead Line: 2016-11-11

 

Tender Detail:

 



1.አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን /የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
 
2.የመኪኖቹን/የንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ (ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪን ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል) በስራ ሰዓት በመገኘት ከጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ማየት ይችላሉ::

 
3.ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውንና የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘውን ፎርም አክሱም ሆቴል ጎን ኮሜት ሕንፃ በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና መ/ቤት ካሣ መምሪያ ሁለተኛ ፎቅ ከጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ::

 
4.ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የያንዳንዱን ተሽከርካሪ/ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ህዳር 2 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ኮሜት ሕንፃ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::


5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ ብር 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች በማስያዣነት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
 
6.ጨረታው ህዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ኮሜት ህንፃ በሚገኘው በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበትይከፊታል::

 
7.ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወይም ንብረት ሙሉ ክፍያ በ5 ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል:: 


ክፍያውን ከፈጸሙ በኊላ በ10 ቀናት ንብረቶቹን ካላነሱ ለሀያ ቀናት በየቀኑ ብር 30.00 /ሰላሳ ብር/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከፍለው ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል::

 
8.ለጨረታ ከቀረቡትተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ዓይነት የስም ማዛወሪያ፣ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል::

 
9.ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-616741 ወይም 0116187000/6632947 በመደወል ወይም በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል::

 
10.መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 
11.ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው::


ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም::