Tenders

 

Type: Services

 

Organization: ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Dead Line: 2016-11-24

 

Tender Detail:

 

 

 

 

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ (ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)

 

  1. የዶክመንተሪ ፊልም ስራ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተጨራቾች የዶክመንተሪ ፊልም ለመስራት ሰነዱ ላይ በተገለጸው ፊልም ስራ መሳሪያ መጠቀም የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ እለት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ሃዋሳ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 5,000 (አምስት ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ከሲፒኦ ውጪ የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ማስከበሪያ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 15/2009ዓ.ም ድረስ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ህዳር 15/2009 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተዘግቶ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በዚህ ቀን 8፡30 ሰዓት በኮሌጅ ህንፃ ግ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታሉ፡፡
  7. በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው ሲሳተፍ የተጨማሪ መገምገማያ መስፈርት የሚየሳየውን ሰነድ ለብቻ በማሸግ ማቅረብ ይናርበታል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ  ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  9. ስልክ ቁጥር፡-  046  212  01 20  /  046  820  92  88
  10. ሀዋሳ ዩኒቭርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ