Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ

Dead Line: 2016-12-18

 

Tender Detail:

 

 

 

 

የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ የክልሉን ህዝብና የልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት በማንቀሳቀስ በትምህርትና፣ በጤና፣ በመሠረታዊ ሙያ ክህሎትና ስልጠና እና ስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋጽኦ የማድረግ ተልዕኮን አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሃገር በቀል የልማት ማህበር ነው::

ማህበራችን ለባህር ዳር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል TOYOTA LAND CRUISER HARD TOP ST.WAGON 5 DOORS SEMIL WB, 4WD, DIESEL HZJ76L-RKMRS መኪና ብዛት 1 ከነሙሉ አክሰሰሪው በቀረበው ዝርዝር መግለጫ መሠረት መግዛት ይፈልጋል::

 ስለሆነም፡-

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣

2. የግዥው መጠን ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 412 ማግኘት ይቻላል፣

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ./ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው::

6. ከላይ የተጠቀሱ ነጥቦችን መሠረት በማድረግ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር 412 እና በአዲስ አበባ የሌሎች ክልሎችና ዲያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ላይ ይታሸጋል በ20ኛው ቀን በ8፡30 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ጨረታው የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣

7. ማህበሩ ከቀረጥ ነፃ የመገዛት መብት አለው

8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

 9. በ90 ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪውን ማቅረብ የሚችልና ከአሁን በፊት ለሌሎች ድርጅቶች ያቀረቡበት መረጃ ማቅረብ የሚችል፣

10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጀ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 413 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582200983 /0582266364 እና አዲስ አበባ ቦሌ ማተሚያ ቤት ጐን አልማ ህንፃ 4 ፎቅ ወይም በስልክ ቁጥር 0115512528 በመደወል ማግኘት ይችላሉ:: ማህበሩ