Tenders

 

Type: Information Technology

 

Organization: የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለካሊብሬሽን ማዕከል

Dead Line: 2016-12-22

 

Tender Detail:

 

 

 

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለካሊብሬሽን ማዕከል የሚውል Supply, install, test and Commission of CCTV ግዥ አስመልክቶ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት::

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰአት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኛው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋናው መ/ ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይቻላል::

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ካታሎግ የሦስተኛ ወገን ማረጋገጫ ናሙናና የጥራት ማረጋገጫ (Quality Certificate)፣ በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በጨረታ ሠነድ በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን ይኖርበታል::

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ታሕሳስ 13/2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

7. ጨረታው ታህሳስ 13/2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 c¯ƒ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::

8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቀጥታ ስልክ ቁጥር ዐ114-4ዐ-34-33/34 ማዞሪያ ዐ114-42-22-70/71/72 ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.ዐ114-40-04-71/0114-42-07-46 ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ