Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት

Dead Line: 2016-12-31

 

Tender Detail:

 

 

 

በአፋጻጸም ከሳሽ ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን እና በአፈጻጸም ተከሳሽ እነ አቶ አማኑኤል አዲሱ 2 ሰዎች መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ  በፍርድ ዕዳ ምክንያት በሁለተኛ የአፈጻጸም  ተከሳሽ በአቶ ማቲዎስ በየነ ስም በሀዋሳ ከተማ በዳቶ ኦዳኤ ቀበሌ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘውን መኖሪያ ት የዳቶ አዳኤ ቀበሌ አስ/ር ጽ/ቤት በቁጥር 1448/ዳቶ/08 በሆነው በቀን 11/12/2008 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ገምቶ በላከው መነሻ ዋጋ ብር 250,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሆኖ በድጋሚ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ከ1/4/2009 ዓ.ም ድረስ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ከ1/4/2009 ዓ.ም ጀምረ እስከ 1/5/2009 ዓ.ም ከ4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ 2ተኛ በሚቀጣው በሐራጅ ማስታወቂያ ተወስኗል፡፡

ስለሆነም፡-

  • በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎች ለጨረታው ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 1/4ኘኛ በሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ ፎቅ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 113 በአካል ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ሕጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ በጨረታ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
  • በጨረታው ለተሸነፈ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስለታል፡፡
  • ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ ግቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቹ ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ካላደረጉ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ማስታወቂያ ወጥቶ ጨረታው ይካሄዳል፡፡
  • ጨረታውን አሸንፎ የገንዘብ ተጫራች የስም ዝውውር በፍርድ/ቤቱ ትዕዛዝ ይፈጸምለታል፡፡
  • ጨረታው ሂደት የሚካሄደው ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ከተማ በዳቶ ኦዳኤ ቀበሌ ውስጥ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ እንደሆነ አውቀው በተባለው ጊዜ እንድትገኙ ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚያስችለው የፍ/ብሔር  ችሎት አዟል፡፡
  • የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት