Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በደ/ቡ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የእርሻና ተፈጥሮ ሀ/ል/ቢሮ

Dead Line: 2017-02-09

 

Tender Detail:

 

 

 

 


የደቡብ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ለቡኢ ኖራ ማምረቻ ማዕከል አገልግሎት የሚውል 700,000 ኖራ መሰብሰቢያ ከረጢቶችንና 300 መስፊያ ክሮችን አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በንግድ ዘርፋ የታደሰ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢነትና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ለመጫረት ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5 % ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና የዕቃውን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ይህ የጨረታ ማታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ  ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የመጫራቻ ሠነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሠነዶችን በአንድ ፖስታ በማዘጋጀት በቢሮው ግዥ ፋይ/ንብ/አስ.ቢሮ ቁጥር 7 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫራቻ ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው ሣጥን የጨረታወወው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫቾች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈት ሥነ-ስርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
  7. ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. በደ/ቡ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የእርሻና ተፈጥሮ ሀ/ል/ቢሮ
  9. ለበለጠ መረጃ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዓርብ ጥር 19 ቀን 2009 ዓ.ም ይመልከቱ፡፡