Catagory Lists
Type: Garment
Organization: በደቡብ ክልል በካፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
Dead Line: 2017-02-12
Tender Detail:
በደቡብ ክልል በካፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2009 ዓ.ም በጀት ዘመን በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ለአገ/ት የሚውል የሠራተኞች የደንብ ልብስ ከህጋዊ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 01 የደንብ ልብስ
ስለዘዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
ሀ. የዘመኑን ግብር የከፈሉነትን ማስረጃና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
ለ. የቲን ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
ሐ. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
መ. ቫት ተመዝጋቢ የሆነና የምዝገባ ሰርተፍርኬት ያላቸውን ያካትታል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ለተከታታይ ለ15 ቀናት ጊምቢ ወ/ፋይ/ኢ/ጽ/ቤት ግዥና ን/አስ/ር በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ 5000 ብር ከጨረታ ሰነድ ጋር በማዘጋጀት ለጊምቦ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በየዕቃው ዝርዝር ሰነድ ላይ በመፃፍ ሰነዱን ለየብቻው ሁለት ቦታ በየዕቃው ዓይነት በሰም/በሙጫ/ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4 ሰዓት ተኩል ላይ ይከፈታል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም በዓል ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው በተመሳሳይ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን አያስቀረውም፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ 047 222 00 55/ 52/54 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በደቡብ ክልል በካፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ዑፋ