Catagory Lists
Tenders
Type: Construction
Organization: በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
Dead Line: 2017-02-13
Tender Detail:
በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለማዘጋጃ ቤት ቀጠና 05 እና 03 የሚያገኝ መሸጋገሪያ ድልድይ የጉልበት ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ ለስማራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ አመልካቾች በመንግስት ግዥ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት ፡-
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት፤
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር(tin number);
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤
- ከሽያጭ ዋጋ ላይ የመንግስት ግብር 2%ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤
- ደረጃ 9 Bc/Gc እንዲሁም የግንባታ ፈቃድ ያለው/ላት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናሉን እና ፎቶ ኮፒ በመለየት በአንድ እናት ፖስታ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ በቁ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአየርላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ተከታታይ የስራ ቀናት ይ ሆናል፡፡
- ተጫራቾች በቁ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የሥራ ዝርዝር የሚገልፀውን የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ 2.5%ከጠቅላላ ዋጋ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሣጥን የሚታሸገው የጨረታው ማብቂያ በ15ኛው ቀኑ ከቀኑ በ11፡30ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡00ሰዓትተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ወይም የተጫራቾቹ ወኪል ያለመገኝት ጨረታውን መከፈትን አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላው ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10%ማስያዝ አለበት፡፡
- 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 046 459 03 93
ሞባይል ቁጥር 09 10 28 97 68 ይደውሉ ይጠይቁ፡፡