Catagory Lists
Tenders
Type: Furniture
Organization: በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የሚዛን ማረሚያ ተቋም
Dead Line: 2017-02-14
Tender Detail:
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የቤንች ማጂ ዞን ሚዛን ማረሚያ ተቋም በ2009 ዓ.ም ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ዘመናዊ የእንጨት ማሽን combination machine/ wood work/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ለሚጫረቱባቸው ማሽን በዘርፋ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው
- የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ቲን ነምበር ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሠነዶች ኦርጅናሉን በማመሳከር ኦርጅናሉን ብቻ የእያንዳንዱን ኮፒ ከጨረታው ሰነድና ሲፒኦ ጋር በማያያዝ ማስገባት አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ኢትዮጵያ ብር 150,000 /አስራ አምስት ሺ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ CPO ከጨረታ ሰነዱና ከሰነዶች ኮፒ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- ከሽያጭ ተቀናሽ 2% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 50/ሀምሳ ብር/ በመግዛት የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት ከዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የእንጨት ማሽን ጨረታውን ሲያስገቡ የእንጨት ማሽኑን አይነት በፎቶ ግራፍ የተደገፈ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ሲያቀርቡ የቫት ዋጋ ደምረው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ 10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ይታሸግና በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት በሚዛን ማረሚያ ተቋም ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ማሸነፋ ከተገለጸበት 2 ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል በመዋዋል ያሸነፈበትን ማሽን እስከ ተቋሙ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ አለበት፣
- ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡- በደቡብ ክልል ቤቶች ማጂ ዞን የሚዛን ማረሚያ ተቋም ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0473350092/0473350592/0471350100/0470350061 ደውለው ይጠይቁ
- በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የሚዛን ማረሚያ ተቋም