Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

Dead Line: 2017-02-14

 

Tender Detail:

 



 በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ አገልግሎቶች ለ2009 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አገልግሎት የሚሰጥ

ሎት 1- የትራንዚተር/የጉምሩክ  አስተላላፊነት ስራ

ሎት 2-የአየር መንገድ የጉዞ ቲኬት ወኪል የአገልግሎት ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ስለዚህ በጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ እና ከዚህ  በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የሚያመሟሉ ተጫራቾች ቀርበው  እንዲወዳደሩ ይጋብዛል.

  2. ተጫራቾች በስራ ዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው  የግብረ ከፋይ መለያ  ቁጥር ሰረተፍኬት ያላቸው በአቅራቢዎች ዝርዝርበ web-site በሙያ  ዘርፉ የተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ  የተመዘገቡ መሆናቸውንና  የዘመኑ ስራ ግብር የከፈሉ  በጨረታ እንዲሳተፉ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤

  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር)  በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (CPO)  ብቻ ማስያዝ  አለባቸው፤

  4.  ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 15 (አስራ አምስት) ቀናተ  ውስጥ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር)  በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከኢ.ግ.ም.ኢ.ዋና መ/ቤት በሚገኘበት ከቦሌ ወደ መገናኛ  በሚወስደው የቀለበት መንገድ   በአምቼ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው፣ ፋይናንስና ግዥ ቢሮ ጥር 24 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 8 ቀን 2009ዓም  በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ድር  ጅቶች ኢግምኢ ብግጨ በቁጥር 05/2009 ተብሎ የተዘጋጅው የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

  5. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ ጥቃቅንና አነስተኛ  ተቋማት  የተቋቋሙትን ህጋዊነት ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ ኮፒውን በማስያዝ ያለክፍያ በነፃ  የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፤

  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ አይነት የተወዳደሩበትን ሎት በመግለጽ  በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያ  ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት  እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት  ከላይ በተጠቀሰው   አዳራሽ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፣

  7.  ተጫራቾች አላስፈላጊ የሙስና ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበት ቅፅ ሞልተውና  ፈርመው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን አለባችው፣

  8. የጨረታው  ሳጥን የካቲት 8 ቀን 2009ዓ.ም  ከጠዋቱ 4 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በኢንስቲትዩቱ ዋና መ/ቤት  የመሰብሰቢያ አዳራሽ  በዓል/ ካላንደር/ የሚዘጋ ከሆነ  በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀንና ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፣

  9. ኢንስቲትዩቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

  10. በሌሎች ተጫራቾች  ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፣

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር፡- 251-11 6 460 196/011 6 459 534 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡