Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

Dead Line: 2017-02-15

 

Tender Detail:

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤቱ ሠራተኞች የካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጥ በሕንፃው ላይ የተለያዩ የምግብ፣ የሻይ ቡናና የለስላሳ መጠጥ በማዘጋጀት ለሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት አገልግሎት ውል ለመግባት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ቢሮው ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉ ንብረቶችን ያቀርባል፡፡

ሀ/ በቂ ወንበርና ጠረጴዛ

ለ  / የቫይ ቡና ማሽን

ሐ/ የቁም ፍሪጅ

መ / ቴሌቪዥን 42 ኢንች ከነ ዲሹ

ሠ  የመብራትና የውሃ አገልግሎት ሲሆን

ከተጫራቾች ተሟልቶ መቅረብ ያለበት

  • ተጫራቾች /አሸናፊ ድርጅት / ከዚህ ውጪ ያሉ ለክበቡ የሚያስፈልጉ ማንኛውም ዕቃዎችን ማቅረብ ግዴታ አለበት
  • ለሠራተኞች የሚቀርቡ መስተንግዶዎች ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
  • ተጫራች ለሠራተኛው የሚያቀርበው መስተንግዶ ደረጃውን የጠበቀ በዝቅተኛ ዋጋ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  • መ/ቤቱ ውስጥ ለሚካሄዱ ስብሰባዎች እና ሥልጠናዎች አሸናፊ ድርት ባሸነፈበት ዋጋ ለማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  • መ/ቤቱ ውስጥ ለሚካሄዱ ሰብሰባዎች እና ሥልጠናዎች አሸናፊ ድርጅት ባሸነፈበት ዋጋ ማቅረብ የሚስማማ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • ስለሆነም ተጫራቾች በንግድ ዘርፋ የሥራ ፈቃድና የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃዎችን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
  • ተጫረቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ከቢሮው የሀብት አስተዳደር የሥራ ሂደት 1ኛ ፎቅ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ብር 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር/  የጨረታ ማስረከቢያ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ/ ፕሮፎርማ/ ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ በመሙላት  ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን  ከጠዋቱ 3፡30  ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በቢሮው 1ኛ ፎቅ ሀብት አስተዳደር የሥራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው ሣጥን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በዕለቱ  4 ሰዓት ተጫራቾች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት ከአለ በጅምላ 100 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ሀብት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
  • ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ የስ.ቁ 046 220 42 24 ይጠቀሙ፡፡
  • የሀዋሳ ገ/ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት