Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ

Dead Line: 2017-02-26

 

Tender Detail:

 

 



 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ከደብረ ብርሃን ብርድልብስ ፋብሪካ ከላይኛው አዋሽ አግሮ አንዱስትሪ ፕሮጀክት /አዋሽ/ የተረከባቸውን ፋብሪካ መለዋወጫ ዕቃወችን ያገለገሉ ጎማዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን  ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50.00/ህምሳ/ በመ/ቤቱ ገንዘብ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ማግኘት ይችላል፡፡
  2. ልዩ ልዩ የፋብሪካ መለዋወጫ ዕቃዎችን ደብረብርሃን ብረርድልበስ ፋብሪካ /ደብረብርሃን ከተማ/ በፋብሪካው ግቢ በሚገኙት የመ/ቤቱ መጋዘኞች ያገለገሉ ጎማዎቹን አዲስ አበባ አዋሬ በሚገኘው የመ/ቤቱ መጋዘን የጨረታ ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ መመልከት ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች ለመጫረታ ከሚያቀርበው ዋጋ 10% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (Bid Bound) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲ.ፒ.ኦ/ በመ/ቤቱ ትክክለኛ ስም በማሠራትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታው ላይ የተጫራቾቹን ስምና አድራሻ ለመጫረት የፈለገው ንብረት በመግለጽ እስከ ጨረታው መዝጊያ የካቲት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ቢሮ ቁጥር 20 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ /አዲስ አበባ/ የካቲት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. በቂ የዋስትና የማስከበሪያ C.P.O ያላስያዙ ተጫራቾች ኮሚቴው ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  6. የጨረታው ዋስትና ማስከበሪያው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉ ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊዎች በውጤቱ መሠረት ክፍያ ከፈፀሙ በኃላ ያሸነፋባቸውን ንብረቶች በሚወጣው የማስረከብ ፕሮግራም መሠረት ሳያነሱ ቢቀሩ ለሚፈጠረው ችግር መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  8. መ/ቤቱ ስለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. የመ/ቤቱ አድራሻ፡-
  10. ቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 03፣ የቡና ተክል ልማት ድርጅት ሕንፃ
  11. የስልክ ቁጥር 0114 16 87 96 ፣ 0114 16 87 87 EX- 217
  12. የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ አዲስ አበባ