Tenders

 

Type: Laboratory Equipments & Chemic

 

Organization: አዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

Dead Line: 2017-02-16

 

Tender Detail:

 

 

 




አዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለተለያዩ የትምህርት ክፍል የሚውሉ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ ያላቦራቶሪ እቃዎች እና ኬሚካሎችን በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለሁሉም ግዥዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የ2009 ዓ.ም ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያጋግጥ ፣ ከግብር ሰብሰቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር , ወረቀት  ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ፣ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡት መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈሉ ቃሊቲ ወረዳ 09 ቂሊንጦ ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ከፍ ብሎ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲ ግቢ ህንፃ ቁጥር 24 ዘወትር በሥራ  ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በአንድ የጨረታ ሰነድ ለወጣው ግዥ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል እና ፋይንሻል ሰነድ ኦርጂናል ለየብቻው በተለያየ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በላይ በተራ ቀጥር 2 ላይ በተመለከተው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን በጨረታ ሰነዱ ክፍል ሁለት የተ.መ 21.1 ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው በጨረታ ሰነድ ቁጥር አአሳቴዩ 15/2009 ለወጣው ግዥ ጨረታ የካቲት 08 ቀን 2009 ዓ.ም እንደዚሁም በጨረታ ሰነድ ቁጥር አአሳቴዩ 19 / 2009 ለወጣው የግዥ ጨረታ የካቲት 09 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
  6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
  7. ዩኒቨርሲቲ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቂሊንጦ ቀበሌ ከጥሩነሽ ቤጂነግ ሆስፒታል 3ኬ.ሜ ገባ ብሎ ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ከቃሊቲ መስመር መንገድ ወይም በጎሮ መስመር በአዲሱ ቱሉ ዲምቱ ደ/ዘይት መንገድ በቀላሉ መድረስ ይቻላል፡፡
  9. ስልክ ቁጥር፡- 0118 69 60 94 / 0118 69 61 20