Catagory Lists
Tenders
Type: Autos
Organization: ዌብስታር ትሬዲንግ
Dead Line: 2016-02-25
Tender Detail:
ዌብስታር ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን ያገለገሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሸከርካሮዎች ማለትም
- ዶዘሮች
- ኤክስካቫተሮች
- ሮለሮች
- ቀላል ተሸከርካሪዎች
- ግሬደሮች
- ሎደሮች
በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ አካል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ከሳር ቤት አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ የኦሮሚያ ክልል ቢሮዎች ፈት ለፊት በር ገ/ሊባኖስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 204 ከ03/06/08 ዓ.ም እስከ 05/06/08 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈት መግዛት የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ንብረቶቹን ገላን በሚገኘውና በተለያዩ የማቆያ ቦታዎች ከ04/06/08 ዓ.ም አስከ 15/06/08/ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ገዥ ለሚገዛው ንብረት የጨረታ መስከበሪያ የንብረቱን መነሻ ዋጋ 10 በሲፒኦ ማስያዝ ይተበቅበታል፡፡
- ጨረታው በ17/06/08 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ18/06/08 ዓ.ም 3፡30 በድርጅቱ ጽ/ቤት ተጫራቾች /ህጋዊ/ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ገዥ ያሸነፈባቻ ንብረቶች በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን አጠናቅቆ ንብረቶችን ይረከባ ያነሳል፡፡ በተሰጠው የግዜ ገደብ ንብረቱን የማያነሳ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ የማይመለስ ሆኖ ንብረቶቹ ለድጋሚ ጨረታ ይቀርባሉ፡፡
- ገዥ የስም ማዛወሪያ ሙሉ ወጪውን የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለአሸናፊዎች ከንብረቱ ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች ግን የሚመለስ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊል ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-21-36-80/0911-06-78-41
በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ዌብስታር ትሬጊንግ ኃ.ተ.የግ.ማህበር