Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

Dead Line: 2017-02-15

 

Tender Detail:

 

 




የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ45ኛ እና ለ46ኛ ዙር ስርጭት የተደለደለውን ስኳር ለማጓጓዝ ከዚህ በታች በተጠቀሱት 4 ምድቦች ከፋፍሎ 45ኛ ዙር ከየካቲት 10 ቀን እስከ መጋቢት 09 ቀን እንዲሁም 46ኛ ዙር ከመጋቢት 15 እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2009 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ ወደ ተመረጡ 77 የማከፋፈያ ቅርንጫፎች ለማጓጓዝ ይፈልጋል::

 

ምድብ 1 ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ የሚጓጓዘው መጠን፡ 112,534 ኩንታል (በአንድ ዙር) የማከፋፈያ ቅርንጫፍ ብዛት 23

ምድብ 2 ከፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የሚጓጓዘው መጠን፡ 109,416 (በአንድ ዙር) የማከፋፈያ ቅርንጫፍ ብዛት 21

ምድብ 3 ከመተሀራ ስኳር ፋብሪካ የሚጓጓዘው መጠን፡ 133,128 (በአንድ ዙር) የማከፋፈያ ቅርንጫፍ ብዛት 15

ምድብ 3 ከአዲስ አበባ የስኳር ኮርፖሬሽን መጋዘን የሚጓጓዘው መጠን፡ 44,831( በአንድ ዙር)

በጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች ሁሉ በጨረታው እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል:: ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፅ/ቤታችን የማይመለስ ብር 200.00 ከፍለው በመውሰድ በሚጫረቱበት ምድብ ውስጥ ለተጠቀሱት የማከፋፈያ ቅርንጫፎች ለአንድ ኩንታል የሚጠይቁትን የትራንስፖርት ታሪፍ እስከ የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ኢኢግልድ ዋና መስሪያ ቤት (ቫቲካን ኤምባሲ ፊት ለፊት) የሌሎች ሴክተሮች ግብዓቶች ግዥና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 023 እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ:: ጨረታው የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም በ8፡ 00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል:: በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርቡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ከትራንስፖርት ታሪፍና ከብቃት ማረጋገጫ ማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: አሸናፊ ተጫራቾች በተመረጡበት የጉዞ መስመር ለሚያጓጉዙት የስኳር መጠን በሚከፈላቸው ትራንስፖርት ዋጋ ላይ የሚሰላ የ20 በመቶ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ያስይዛሉ:: ድርጅቱ የስኳር ስርጭቱን በተያዘው ፕሮግራም መሰረት መፈፀሙን ለማረጋገጥ እንዲያስችል የተሻለ ነው የሚለውን አሰራር ለመጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-69-26-47/69-24-39