Catagory Lists
Tenders
Type: Multiple Items
Organization: የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
Dead Line: 2017-03-13
Tender Detail:
የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃወች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት |
የእቃዉ አይነት |
ምርመራ |
1 |
Strong Room Door |
|
2 |
8 Port KVM Switch with LCD Display |
|
3 |
Audio System supply and installation |
|
4 |
Exhost Fan |
|
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልግድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያወች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸዉን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸዉን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎችማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በመቁጠር በ20ኛው ቀን ከቀኑ10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት በባህርዳር ከተማ በሚገኘው የዋናዉ መ/ቤት በ አረጋዉያን ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 23 ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን 2 % ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል ቢድ ጋረንቲ ወይንም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለፀለት በኋላ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 % የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (አንኮንድሽናል ባንክ ጋራንቲ)በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-222-1751 ደውለው መጠየቅ እናዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድህረ-ገጽ (www.awwce.com.et) ላይ ማግኘት ይችላል፡፡
አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
ባህር ዳር፡-