Tenders

 

Type: Electronics

 

Organization: በደቡብ ሬዲዮና ቴልቪዥን ድርጅት አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Dead Line: 2017-03-14

 

Tender Detail:

 

 

 

 

 

በደቡብ ሬዲዮና ቴልቪዥን ድርጅት አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2009 ዓ.ም በጀት ኣመት አገልግሎት የሚሠቱ የሚዲያ ቴክኖሎጂ ዕቃዎችን ለሚዲያ አገልግሎት የሚውሉ ማለትም የሬዲዮ ሰርቬር፣ ቴሌሆስ እና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የተለያዩ መገልገያ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-

 

  1. በዘርፋ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ፣ የነጋዴ መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክሜንት በመለየት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 (አስራ አራት) ተከታታይ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃውን ሙሉ ዝርዝር (specifications) ከጨረታው ሰነድ ጋር ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ በነፃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን የዕቃዎች ዝርዝር (ባህሪይ) (specification) ሙሉ በሙሉ ያሟሉ ዕቃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ፕሮግራም ላይ የድርጅቱን ማህተም፣ ሙሉ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥራቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የመወዳደሪያ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይባቸውንና የዋስትና ጊዜያቶችን ማስቀመጥ ሲኖርባቸውን ዋጋው የሚቆይበት ጊዜያት ጨረታው የተከፈተበት ቀን አንስቶ ከ30 ቀን በታች መሆን የለበትም፡፡
  8. በተጫራቾች ዋጋ አቀራረብ ላይ በመደመር ወይም በማባዛት ስህተት ቢገኝ የተጠቀሰው የነጠላ ዋጋ ወሳኝ ይሆናል፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bound) 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታውን ላሸነፋ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ዋስትና እንደሰጡ ወዲያውኑ የሚመለሰላቸውን ሲሆን፣ ለአሸናፊው ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ከ15ኛው ቀን ጀምሮ የሚከፈላቸው ይሆናል፡፡
  11. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ አካል አቅርቦ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡

 

  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  • የዋጋ ማሰከበሪያ ቼክ (CPO) የኢት.ንግድ ባንክ መሆን አለበት
  • ስልክ ቁጥር ፡- 046 881 36 35 ፋክስ ቁጥር፡- 046 881 09 53
  • በደቡብ /ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት