Catagory Lists
Tenders
Type: Garment
Organization: በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
Dead Line: 2017-03-06
Tender Detail:
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምሥራቅ አዲስ አበባ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ለ2009 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውል፡-
የደንብ ልብስ፡- በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፣
በመሆኑም ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
- የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተተ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የምስክር ወረቀት፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ሁኔታዎቹ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መገናኛ አካባቢ የቀድሞ ለም ሆቴል በስተቀኝ ኮሜት ሕንፃ ቁጥር 2 የሚገኘው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምሥራቅ አዲስ አበባ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 8ኛ ፎቅ ግዢና ፋይናንስ ቡድን አስተባባሪ ቢሮ በአካል ቀርበው መግዛት የሚችሉ መሆኑን፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ታሽጎ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምረ እስከ 1/7/2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 8ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በማስያዝ በመ/ቤቱ ጋረ ውል ይፈራረማል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስልክ፡ +251 11 667 47 31
- በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የምሥ/አ/አ/መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት