Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ሲዳማ ዞን ኮንስትራክሽን መምሪያ

Dead Line: 2017-03-17

 

Tender Detail:

 

 

 

 

በሲዳማ ዞን ፖለስ መምሪያ በ2009 በጀት ዓመት በመምህሪያው ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የጽ/ቤቱን ህንፃ ጥገና ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡በዚሁ መሠረት፡-

 

    1. ደረጃቸው GC/BC- 7 እና ከዚያም በላይ የሆኑ ተጫራቾች በ2008/2009 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የኮንስትራክሽን ሚ/ር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
    2. ተጫራቾች የ2008 በጀት ዓመትን ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
    3. በማንኛውም ቦታ ግንባታ ሂደት ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጠው ተቋራጮ የሆነ፣
    4. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችና መሳሪያዎች በግላቸው አጓጉዘው ለሚሠሩና ለሚያጠናቅቁ፣
    5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሸህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ የሚችሉ፣
    6. ተጫራቾች ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.እ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ሲዳማ ዞን ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት ከፍለው የከፈሉበትን ሰነድ በመያዝ በሲዳማ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ መውሰድ ይችላሉ፣
    7. ማንኛውም ተጫራቾች ከወድድሩ በፊት የሥራ ሣይት በራሱ ወጭ አይቶ ማረጋገጥ አለበት፣
    8. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ቢድ ቦርድ ኦርጅናሉና ሁለት ፎቶ ኮፒዎችን ለየብቻቸው በሰም በታሸጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
    9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
    10. የቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፣
    11. አሸናፊው ተጫራቾች ከባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፣
    12. አሰሪው ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
    13. ማሳሰቢያ፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
    14. የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ሲዳማ ዞን ኮንስትራክሽን መምሪያ